የፕሮግራም ስም የፕሮግራም ይዘት የስርጭት ቀን እና ሰዓት
  የተለያዩ አገራዊና አለምአቀፋዊ ክስተቶችን/መረጃዎችን በትኩሱ ለተመልካቾች ያደርሳል፡፡ሰበር ዜናዎችን፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይታዘባል፤ ይመረምራል፤ ህብረተሰቡንና የሚመለከታቸውን አካላት ያናግራል፤ የራሱን አስተያየት ያክላል፡፡ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከረፋዱ 4፡00 – 4፡30
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ እኩለ ቀን ከ6፡30 – 7፡00
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከምሽት 1፡30 – 2፡00
በድጋሚ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ማታ ከ4፡00 – 4፡30
     
  ሲኒማ፣ የሙዚቃ ድግስ፣ የግጥም ምሽት፣ መጽሐፍት ምረቃ፣ የስዕልና ፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን፣ ባዛር፣ የባለሙያዎች ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የምግብ ፌስቲቫሎች …ወዘተ ያሉ ወቅታዊና ማህበራዊ ዝግጅቶችን /ኢቬንተስ/ ሐሩ ፕሮግራም  እየተከታተለ ለህብረተሰቡ ያቀርባል፡፡  

ቅዳሜ ከ11፡00 – 12፡00

     
   

በሰው ልጆች ብዙም ያልተለመዱና ጥቂቶች ብቻ የሚያውቋቸውን የዓለማችንን አስገራሚ ስፍራዎች የምንመለከትበት የዶክመንታሪ ፕሮግራም ነው፡፡

 

ቅዳሜ ምሽ ከ3፡00 – 4፡00

     
 

“ኦዳ” ከፍተኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆነው የሚያልፉ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ነጻ የሆነ የቡድን ውይይት የሚደረግበት ቶክ-ሾው ነው፡፡ የተለያየ አቋም፣ የተለያ አተያይ፣ በሚነሳው ጉዳይ ላይ የተለያየ ስሜት ያላቸው ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ፣ በነጻ ፕሬስና በተለያዩ መድረኮች አቋማቸውን በግልጽና በድፍረት በማሰማት የህብረተሰቡን አስተሳሰብ በመቅረጽ የሚታወቁ ግለሰቦች ይወያዩበታል፡፡

 

 

 

እሁድ ከረፋዱ ከ5፡00 – 6፡00

 

     
   

በየጊዜው ከተለያዩ የዓለም ክፍል በየሽርፍራፊ ሰከንዶች ከሚሸጋገረው የመረጃ ፍሰት ጋር አብረው መጓዝ እንዲችሉ የሚያግዝ የመረጃ ፕሮግራም ነው፡፡

 

Coming soon

     
   

የመንግስት ባለስልጣናትን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን፣ ባለሐብቶችን፣ የኃይማኖት አባቶችን… ወዘተ ጨምሮ በአገራችን ውስጥ በየዘርፉ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን ፊት-ለፊት አቅርቦ በቃለ ምልልስ ጠለቅ ያሉ ጉዳዮችን አንስቶ የሚያነጋግር፣ የሚያጨዋውትና እንደአስፈላጊነቱም የሚሞግት ፕሮግራም ነው፡፡

 

 

ቅዳሜ ከሰዓት ከ8፡00 – 9፡00

 

     
   

ህጻናት የልጅነት ዘመናቸውን በማይረሳ አስደሳች ጨዋታ እንዲያሳልፉ የሚያግዙ፣ ማንነታቸውንና ባህላቸውን አውቀው ለራሳቸውና ለአገራቸው መልካም ነገሮችን እንዲሰሩ የሚያግዝ ፕሮግራም ነው፡፡

 

ከሰኞ እስከ አርብ ምሽት ከ12፡00 እስከ 12፡30

 

     
 

የተመረጡ የአገር ውስጥና የውጪ አገራት የሙዚቃ ቪዲዮዎችን የሚያቀርብ ፕሮግራም ነው፡፡

 

 

 

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ምሽት ከ12፡30 – 1፡30

 

     
   

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ ስፖርታ ኩነቶች በስፋትና በጥልቀት ከሰፊ ትንታኔ ጋር ለተመልካች የሚደርሱበት ፕሮግራም ነው፡፡

 

ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 6፡40 እና ምሽት 1፡40

ቅዳሜ ከቀኑ 6፡40

     
   

በአገራችን ውስጥ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው ለሀገራችን የላቀ ሚና የተጫወቱ አካል ጉዳተኛ ግለሰቦችን ማክበር እንዱሁም የሰሩትን ስራ እውቅና የሚሰጥበት ፕሮግራም ነው፡፡ በተጨማሪም ከስራ ህይወታቸው በተለየ ማህበረሰቡ የማያውቀውን ገንቢ እና አስተማሪ መረጃበመሰብሰብ ለህብረተሰቡ የሚያቀርብ ነው፡፡ ሌሎች ተያያዥ የቴክኖሎጂ መረጃችም ይዳሰሱበታል፡፡

 

እሁድ ከጠዋቱ 3፡30 – 4፡00

     
   

በመዲናችን የሚገኙ የተለያዩ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች ጋር በመዘዋወር የሚደረግ የምግብ ዝግጅት ፕሮግራም ነው፡፡

 

ሰኞ ምሽት 2፡00 – 2፡15

እረቡ ምሽት 2፡00 – 2፡15

አርብ ምሽት 2፡00 – 2፡15